ማጠቃለያ

በኮቪድ19 ምክንያት በሲቪክ ማእከላችን የሚሰጥ የነበረው ፊት ለፊት አገልግሎት ተዘግቷል። ምክር ቤቱ የሲቪክ ማእከሉን እንደገና ከመክፈቱ በፊት ተጨማሪ አገልግሎቶችን በመስመር ላይ ለማንቀሳቀስ፣ ዲጂታል ተደራሽነት ችግሮች ያሉባቸውን የሚደግፉ እና ማህበራዊ የርቀት እርምጃዎችን የሚያስተዋውቁ ዕቅዶችን እያወጣ ነው። በዲሴምበር 2020 እንደገና በአዲሱ አገልግሎት ለመጀመር አቅደናል ስለሆነም ስለእኛ እቅድ ምን እንደሚያስቡ መስማት እንፈልጋለን።

ለምን ለመቀየር አሰብን

ነዋሪዎቹ የሲቪክ ማእከሉ በጣም ጫጫታ የበዛበት፣ በጣም ክፍት የሆነ እና የት መሄድ እንዳለባቸው ለማወቅ ከባድ እንደነበር ገልፀውልናል። የጎብኝዎች ቁጥርም ብዛት ያለው በመሆኑ መጠን ከፍተኛ እገዛን ለሚፈልጉ ሰዎች የማያቋርጥ ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት አስቸጋሪ ሆኖብን ነበር ፡፡

ዝግ በነበረበት ወቅት, ምክር ቤቱ በዋናነት ነዋሪዎች እና ንግዶች በአካል መገኘት ሳያስፈልጋቸው የስልክ እና የቪዲዮ ጥሪዎችን, እና ኢሜይሎች በኩል ሊገናኙ የሚችሉበትን መንገዶች አስተዋውቋል። እኛ ደግሞ በድርህረ ገጻችን ላይ እየሰራንና ደንበኞች የሚፈልጉትን መረጃ በፍጥነት እንዲያገኙ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ቀላል እንዲሆን የጥሪ ማዕከላችንን እያሻሽልን ነው።

ሰዎች ይበልጥ አመቺ በሆነላቸው ቁጥር ከቤት የበለጠ ምስራት ይችላሉ ብለን እናምናለን፣ እንዲሁም በድረገጽ እና በስልክ በኩል የሚቀርቡት አገልግሎቶች ለምክር ቤቱ ፊት ለፊት ከማቅረብ በጣም ስለሚረክስ ምክር ቤቱ ሌላ ለምክር ቤት አባላቱ የሚያስፈልግ አገልግሎት ላይ ገንዘቡን እንዲያውል ያስችለዋል።

ለመለወጥ ያቀድነው

እቅዳችን አዲሱ ፊት ለፊት አገልግሎት በተለይም ለሚከተሉት አይነት ሰዎች እንደሚሰጥ ነው፡
  • የምክር ቤት አገልግሎቶችን በድረገፅ ወይም በስልክ መድረስ በጣም አስቸጋሪ ሚሆንበት ወይም የማይችሉ፣ እናም እንግሊዝኛ የመጀመሪያ ቋንቋቸው ያልሆነ ፣ በአእምሮ ጤና ሁኔታዎችን ፣ በመማር ችግሮች ፣ በስሜት ሕዋሳት ወይም በንግግር እክል ምክንያቶች አንድ ለአንድ አንድ ድጋፍ የሚፈልግ ሰው።
  • ቤት ውስጥ ኮምፒተር እና ስካነር የሌላቸው ወይም እነሱን ለመጠቀም እገዛን የሚፈልጉ
  • የመኖሪያ ቤት እጦት አደጋ ላይ የሆኑ
  • ከምክር ቤት አገልግሎት ጋር ቀጠሮ ይያዙ
ከዚህ በፊት ከነበረው ይልቅ ለደንበኞች አነስ ባለ ቡድን ከፍተኛ ጥራት እና የግል አቀራረብ ለመስጠት ያስችላል.

የሚከተሉትን እንድናቀርብ የሲቪክ ማእከሉን ምድር ፎቅ እንደገና ለመገንባት እና በሠራተኞቻችን እና በቴክኖሎጂው ላይ በይበልጥ ለመስራት አቅደናል።
  • ተቀባይ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተረጋጋ አካባቢ
  • ነገሮችን እንዴት እንደምናከናውን የሚያሳይ ግልፅ ተግባቦት እና ምልክት
  • ጥራት ያለው የደንበኛ እንክብካቤን የሚሰጡ እና ለተለያዩ የግለሰቦች ፍላጎቶች ጥሩ ምላሽ የሚሰጡ በከፍተኛ የሰለጠኑ ሰራተኞች
  • ደንበኞች አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲጠቀሙ ለማስቻል የተሻሻለ ቴክኖሎጂ
  • የአካል ጉዳተኛ ሰዎች የመንቀሳቀስ ፍላጎትን የሚያሟላ ቦታ
  • የቫይረሶች ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችል እና ደህንነትዎ የሚጠበቅበት ቦታ
ይህ የዳሰሳ ጥናት መጠይቅ ከላምቤዝ ካውንስል አገልግሎቶች ጋር ስለሚኖሮት ግንኙነት፣ ስለሚጠቀሙባቸው የግንኙነቶች ስልቶች እና ይህን አገልግሎት እና ቦታ አቀማመጥ ዲዛይን ላይ የሚፈልገውን ለውጥ በተመለከተ ጥያቄዎችን ይጠይቆዎታል። መጠይቁ ከ 15 ደቂቃዎች በላይ ጊዜ አይወስድም እና የመጠይቁን ውጤት እቅዳችንን የበለጠ ለማሻሻል እንጠቀምበታለን። ስለተሳተፉ እናመሰግናለን!

T